Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቪሳት አገልግሎት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በ23 የክልሉ አካባቢዎች የቪሳት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የቪሳት አገልግሎት በሀገር ውስጥ የመንግስትና ህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስምምነት መድረኩ ላይ የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከፍተኛ አመራር አካላት፣ የቪሳት አገልግሎት ተደራሽ የሚደረግባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች አመራር እንዲሁም በኢትዮ ቴሌኮም የሶማሌ ክልል ሪጅን ከፍተኛ አመራር አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተገኝተዋል።

የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብዲፈታህ ሼክ ቢሂ የቪሳት አገልግሎት ተደራሽ የሚደረግባቸው 23 የክልሉ አካባቢዎች፥ ቋሚ የቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽ እስከሚደረግላባቸው በጊዜያዊነት ለመንግስትና ለህዝብ የኢንተርኔትና የስልክ ጥሪ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ መሀመድ የሱፍ ሮብሌ በበኩላቸው የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ የክልሉ አካባቢዎች የመንግስትና ህዝብ አገልግሎት እያስተጓጎለ ስለሆነ፣ የክልሉ መንግስት ችግሩን በአግባቡ ለመቅረፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.