Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት በአልጄሪያ ከሚገኝ መድሃኒት አምራች ጋር በኢትዮጵያ መሰማራት በሚችልበት አግባብ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሀገሪቱ ከሚገኝ የመድሃኒት ማምረቻ ጋር ኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት መዳረሻው እንዲያደርግ ያለመ ውይይት አካሄዱ፡፡

አምባሳደሩ የመድሃኒት ማምረቻ ዘርፍ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ካለው ከፍራተር ራዜስ የፋርማሲቲካልስ ኩባንያ ፕሬዚዳንትና ባለሃብት ዶክተር አብደልሃሚድ ሸርፋዊና ባልደረቦቻቸው ጋር ነው የተወያዩት፡፡

ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል ግንዛቤ አግኝተው ኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት መዳረሻቸው እንዲያደርጉ ማበረታታትን ዓላማ ያደረገ ውይይት ማካሄዳቸው ነው የተገለጸው፡፡

አምባሳደሩ ለኩባንያው ባለቤትና የሥራ አመራር አካላት ባደረጉት ገለጻ የፋርማሲዮቲካል ዘርፍ በመንግሥት ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው አብራርተዋል፡፡

በዘርፉ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የገበያ እድል እና በመንግስት ስለሚቀርቡት የተለያዩ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ጥቅሎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያመረቱትን ምርት ለመሸጥ በኢትዮጵያ ካለው ሰፊ ገበያ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ስትራቴጂካዊ መገኛ ስፍራ ተጠቅመው ወደ ተለያዩ ገበያዎች በቀላሉ መድረስ እንደሚቻልና የአጎዋና መሰል ከቀረጥ ነጻ የገበያ ዕድሎች ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም ተናግረዋል።

ባለሃብቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ዘርፉን ለማሳደግ እያደረገች ያለውን ጥረት እና ያለውን ከፍተኛ የገበያ እድል አድንቀዋል፡፡

በዘርፉ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚያስችል የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት በቅርቡ እንደሚያካሄዱም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ በኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችሉ ውይይቶችን በሀገሪቱ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.