በትግራይ ክልል ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ እየቀረበ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታ እየቀረበ መሆኑን የአደጋ እና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ተናግረዋል።
ህግ ከማስከበሩ በፊት በክልሉ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ ፈላጊ እንደነበሩ ያነሱት ኮሚሽነሩ ህግ ማስከበሩ ከተጠናቀቀ በኋላ 780 ሺህ ዜጎች ተጨማሪ እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል ብለዋል።
በዚህም እስከ ትናንት ድረስ ለ2 ሚሊየን 7 ሺህ ዜጎች እርዳታ መቅረቡን ገልጸዋል።
200 ሺ ኩንታል ስንዴ እና የመንግስት 690 ሺህ የልማታዊ ሴፍቲኔት ስንዴ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን በመጥቀስም በቅርቡ ለህብረተሰቡ ይሰራጫል ብለዋል።
እርዳታ በማከፋፈሉ ረገድ የትራንስፖርት እና እርዳታን በፍትሃዊነት የማከፋፈል ችግር መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
አሁን ላይም ችግሩን ማህበረሰቡን እና የትራንስፖርት ድርጅቶችን በማስተባበር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በብስራት መለሰ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!