Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዮቹ ሁለት ወራት እስከ 9 ሚሊየን የኮቪድ19 ክትባት ወደ ሃገር ቤት ለማስገባት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጋቢት ወር መጨረሻ አልያም ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ እስከ 9 ሚሊየን የኮቪድ19 ክትባት ወደ ሃገር ቤት እንዲገባ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በክትባቱ እና “እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ” በሚሉት ዘመቻዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ለክትባቱ በዋናነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎችን የመለየት ስራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በዚህም የጤና ባለሙያዎች፣ የማህበራዊ ጤና ሰራተኞች፣ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ነው ያሉት፡፡

በምስክር ስናፍቅ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.