ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ወራት 622 ሚሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት 622 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ገቢው የተሰበሰበው ከውሃ የአገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ከልዩ ልዩ የገቢ ርዕሶች መሆኑ ታውቋል፡፡
በባለሥልጣኑ ጥናት ዕቅድና በጀት ሃላፊ አቶ በዓለምላይ ባህሩ ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 798 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የዕቅዱን 78 በመቶ ማሳካት ችሏል ብለዋል ፡፡
አፈጻጸሙ ከእቅዱ አንጻር ዝቅ ቢልም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ13 ሚሊየን ብር ብልጫ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡
በባለስልጣኑ በስድስት ወራት ከ96ሚሊየን ብር በላይ ያልተሰበሰበ ውዝፍ ሂሳብ እንዳለው ገልፆ ከዚህ ውስጥ ከ50ሺህ ብር በላይ ውዝፍ ያለባቸው 212 ደንበኞች መኖራቸውም ማስታወቁን ከባለስልጣሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!