Fana: At a Speed of Life!

“ሰብአዊነትና ፍቅር ለትግራይ እና ለመተከል” በሚል መሪ ቃል ድጋፍ ማሰባሰብ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)”ሰብአዊነትና ፍቅር ለትግራይ እና ለመተከል” በሚል መሪ ቃል ድጋፍ ማሰባሰብ ተጀምሯል።

ግሎባል አላየንስ የሰብአዊ ድጋፍ ጥምረት፣ የኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች ማህበር፣ የትግራይ እና የመተከል ድጋፍ አሰባሳቢ በጎ ፈቃደኞች እና የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር በጋራ በመሆን ድጋፉን ለማሰባሰብ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በዚህም በአዲስ አበባ በጣይቱ ሆቴል እና በኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር፤ በክልል በቀይ መስቀል ማህበር ዋና ጽ/ቤት እንዲሁም በክልል ከተሞች በቀይ መስቀል ማህበር ጽህፈት ቤቶች የዓይነት ድጋፍ በመለገስ የዜግነት ግዴታን መወጣት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀይ መስቀል ስም በተከፈተ የባንክ ቁጥር 10003277016559 ከ5 ብር ጀምሮ ድጋፍ እንዲያደርጉ የተጠየቀ ሲሆን፥ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በግሎባል አላየንስ በተከፈተ ጎፈንድሚ እንዲረዱ የድጋፍ አሰባሳቢ ህብረቱ መጠየቁን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.