ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለስራ ጉብኝት ቡሩንዲ ገቡ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቷ ቡጁምቡራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቭሪስቴ እንዴይሺምዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዘዳንት ሣህለ ወርቅ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያና ቡሩንዲ የቆየ ወዳጅነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ መስኮች የሚያደርጉትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራም ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቡጁምቡራ ከተማ በሚገኘው የቡሩንዲ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጀግኖች ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!