ም/ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ሊንዴ ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ሊንዴ ጋር በስልክ ተወያዩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ስራ በስኬት መጠናቀቁን አስረድተዋል።
የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እና የመልሶ ግንባታ ስራ በክልሉ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
መንግስት ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን መለየት መቻሉን ገልጸው ድጋፍ ማቅረቡም እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል።
ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የህክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት ከ92 ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሁኑን አብራርተዋል።
በክልሉ 26 የሚሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች በርካታ አካባቢዎች ላይ አቅርቦቱ ተደራሽ እንዲሆን እየሰሩ እንዳለም ነው የጠቆሙት።
ድጋፍ የሚሹ ወገኖች እርዳታ እንዲያገኙ መንግስት አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግም አንስተዋል።
ኤርትራውያን ስደተኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ እየኖሩ እንዳለም ነው ያነሱት።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአውሮፓ ህብረት በክልሉ ስላለው እውነታ ያለመረዳት መንግስትን እንደሚያሳስበውም አስረድተዋል።
አቶ ደመቀ መጪው ሀገራዊ ምርጫ ግልጽ፥ ተአማኒ፥ አሳታፊ፥ ተቀባይነት ያለው እና ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ሚኒስትሮቹ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ ተወያይተዋል።
የስዊድኗ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ሊንዴ ስለተሰጣቸው ማብራሪያ አመስግነዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!