Fana: At a Speed of Life!

የ”ቱባ ወግ የአድዋ ድል ተምሳሌት” የውይይት መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ125ኛው የአድዋ ድል በዓል አከባበር አንድ አካል የሆነው “የአድዋ ድል ተምሳሌትነት” በሚል ርዕስ የታሪክ ምሁራንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የተገኙበት ውይይት ተካሄደ፡፡

ውይይቱ “ቱባ ወግ” በሚል በታሪክ እና በሀገር በቀል ዕውቀቶች ዙሪያ የሚደረገው ወርሀዊ ውይይት ሲሆን፥ የመነሻ ሀሳቦች ቀርበዋል።

በመድረኩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው የአድዋ ድል በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ መጻፍ ያለበት የጋራ ማንነት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአድዋ ድል ለመላው የጭቆና ቀንበር ለተጣለባቸው የይቻላልን መንፈስ ያላበሰ በመሆኑ እሴቱን በሚገባ ማወቅ እና ማሳወቅ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

አያይዘውም ስርአተ ትምህርቱ በቀጥታ ከውጭ የተቀዳ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በጀግንነት ያለፉባቸውን ታሪኮች ብዙ እንደማያውቋቸውና ይህም እንደጎዳቸውም አውስተዋል፡፡

የትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚመስል የህብረ ብሔራዊነት ታሪክ ትምህርትን ልጆች እንዲማሩበት የታሪክ ምሁራን ሕብረት በመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የአድዋ ድል ለመላው አፍሪካውያን ለነፃነታቸው እንዲተጉ ያደረገ ታላቅ ድል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአድዋ ድል የነፃነት ብቻ ሳይሆን የእውነት ድል መሆኑን በዘመናዊ መሣሪያ ታጥቆ የመጣውን ወራሪ ኃይል ያሳፈረው የኢትዮጵያ ሠራዊት በባዶ እግሩ ታግሎ ድል ማድረጉ ብዙ የሚነገርለት መሆኑም ተነስቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም የመላው የጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌትነት ያለው ታሪካዊ ክስተት እንደሆነና ለነጮች አውሮፓውያን ውርደታቸው እንደሆነ በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ተጠቅሷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.