የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በመተከል ዞን ለደረሰው ግድያና ውድመት ይቅርታ ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በመተከል ዞን ለደረሰው ግድያና ውድመት ይቅርታ ጠየቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጉባኤ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
ጉባኤው በአሶሳ ከተማ በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የሠላም ሁኔታ ላይ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በዚህም በክልሉ መተከል ዞን በደረሰው አሳዛኝና ዘግናኝ ማንነት ተኮር ግድያና ውድመት ፓርቲው ይቅርታ ጠይቋል፡፡
የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ‘ብልፅግና አሀዳዊ ነው’ በሚል የሀሰት ትርክት ከሁለት ቦታ በመርገጥ ህዝብን ሲበድሉ የነበሩ አመራሮች መኖራቸውም ተገምግሟል፡፡
በቀጣይ የህግ የበላይነትን በማስከበር በወንጀል የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎችም ተጠያቂ እንደሚሆኑም ተጠቁሟል።
የፓርቲውን እሴትና መርህ በማክበር የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም በአቋም መግለጫው ማሳወቁን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!