የተመድ የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጠናዊ ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ መቐለ ገብተዋል
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጠናዊ ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ መቐለ ገብተዋል።
ዳይሬክተሯ መቐለ የገቡት በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በመንግስት እየተካሄደ ያለውን የመልሶ ግንባታ ለመደገፍ የሚያስችል ጉብኝት ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
በቆይታቸውም ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የተመድ የልማት ፕረፐግራም ለትግራይ ክልል ሶስት ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!