Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ወለጋ ዞን በ33 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ወለጋ የተለያዩ ወረዳዎች በ33 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሰሞኑን በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡

በዚህም 33 የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገልጿል፡፡

እርምጃ ከተወሰደባቸው በተጨማሪ 8ቱ ከነሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

የዞኑን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በኦነግ ሸኔ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ፖሊስ በመግለጫው አንስቷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.