በሶማሌ ክልል ሺንሌ ወረዳ በ200 ሚሊየን ብር የተገነባ ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሺንሌ ወረዳ በ200 ሚሊየን ብር የተገነባ ፋብሪካ ተመርቋል፡፡
የሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ጉዳዮችና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዲሰላም ዩሱፍ፥ በሶማሌ ባለሀብት ሃጂ ኢልሚ ጌሶድ በሲቲ ዞን ሺንሌ ከተማ በ200 ሚሊየን ብር የተገነባ ፋብሪካ መመረቁን ተናግረዋል።
ፋብሪካው እንደፍራሽ፣ የውሃ ቧንቧ ቱቦዎችና ሌሎች ጥሬ ዕቃዎችን የሚያመርት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፋብሪካው ባለቤት ሃጂ ኢልሚ ጌሶድ ፋብሪካው በአንድ ሰዓት ውስጥ ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ ፍራሾች የማምረት አቅም እንዳለው ጠቅሰው ለበርካታ የአካባቢው ወጣቶች የሥራ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የሶማሌ ክልል ባለሃብቶችና ዳያስፖራ መዋዕለ ንዋያቸውን በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች በማፍሰስ የክልሉን የመሰረተ ልማት ተሳትፎ እያሳደጉ እንደሚገኙ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!