Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጎልድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጎልድ ጋር የበይነመረብ ውይይት አካሄዱ።

በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ሂደት ተከትሎ እየተደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ክልሉን መልሶ የማቋቋም ሰፊ ጥረት ተወያይተዋል፡፡

በክልሉ በሚገኙ 36 ወረዳዎች በተከፈቱ 92 የምግብ ስርጭት ጣቢያዎች እየተካሄደ ስላለው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ ስርጭት ሂደት ተወያይተዋል፡፡

ተጨማሪ ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከአጋር አካላት ጋር የመስራት የትብብር አቅጣጫዎች ይበልጥ ተጠናክረው የሚቀጥሉበት አግባብ ላይ በዝርዝር መወያየታቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

በሁለቱ ሀገሮች መካከል የቆየውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ የሚሰራ መሆኑን እና ለዚህም ከስምምነት መደረሱን ወይዘሮ ሙፈሪያት ገልፀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.