ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ከውጭ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ሊሳተፉባቸው በሚችሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ከውጭ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ሊሳተፉባቸው በሚችሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዳያስፖራዎች በተለይ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ያላቸው አስተዋጽኦ የተገደበ ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።
ለዚህም ዳያስፖራዎቹ ያላቸው አቅም ውስን መሆኑና እነሱን ሊያስተናግዱ የሚችሉ በቂ ፓኬጆች አለመኖራቸውን በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡
ዳይሬክተሯ አያይዘውም ለእነዚህ ዜጎች ምቹ ሁኔታን መፍጠር ከተቻለ ከስደት መልስ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መውጫ መንገድ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ራሳቸውንና ሃገራቸውን እንዲጠቅሙ ማድረግ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በዚህ የምክክር መድረክ ማጠቃለያ ላይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በትውልድ ሀገራቸው በንግድና በኢንቨስትመንት ሊያሳትፍ የሚችል ልዩ የኢንቨሰትመንት አማራጭ በፓኬጅ መልክ በሚዘጋጅበት ሁኔታ ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ታውቋል፡፡
መንግስት በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ባመቻቸው እድል መሰረት በርካታ ዳያስፖራዎች በኢንቨስትመንት፣ በንግድና በቱሪዝም ዘርፎች በመሰማራት ራሳቸውንና ሃገራቸውን በመጥቀም ላይ ይገኛሉ፡፡
በዘመን በየነ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!