Fana: At a Speed of Life!

ከሱዳን የሙዚቀኞች ማህበር ተወካዮች ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካርቱም የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሱዳን ሙዚቀኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ሃይደር ሀሚት፣ የማህበሩ አባል ከሆኑት ኢማድ ሁሴን እና ሲዲቅ ሞሂ ጋር ውይይት አደርገዋል።
በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ይበልጣል የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር በማንሳት በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ጠንካራና ዘርፍ ብዙ ግንኙነት ለማጎልበት የኪነ ጥበብ ሰዎች ሚና የጎላ መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህ አኳያ ኤምባሲው ከሱዳን የሙዚቀኞች ማህበር ጋር በቅርበት በመስራት የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጎልበት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
እንዲሁም በኢትዮጵያና ሱዳን ወቅታዊ ግንኙነት በተለይም በጋራ ድንበሩ እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
የሙዚቀኞች ማህበር ተወካዮች በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት ሕዝቦች መካከል የቆየውን ግንኙነት ለማጎልበት በሙያቸው ከኤምባሲው ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.