Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የ6 ወር የሥራ አፈጸጸም ግምገማ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልጽግና ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የበጀት ዓመቱን የ6 ወር የሥራ አፈጸጸም ግምገማ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ  አጠናቋል።

በፓርቲው የሴቶች ሊግ  ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም አበበ ÷ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ አያይዘውም በክልሎች መካከል የሚስተዋለውን የአፈጻጸም ልዩነቶች ለማጥበብ ጽህፈት ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት በብልጽግና ፓርቲ የፓለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ክትትል ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ ሴቶች ለማህበራዊ ትብብር ቅርብ ስለሆኑ ለብልጽግና ራዕይ መሳካት ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ሃላፊው አያይዘውም ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ በምታካሂዳቸው ፕሮጀክቶች የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አሁን ካለው የበለጠ ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ምርጫ ፍጹም ነጻ፣ ተዓማኒና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሴቶች በየአደረጃጀታቸው ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ዶክተር ዓለሙ አሳስበዋል፡፡

የ6 ወር የሥራ አፈጸጸም ግምገማ ሲጠናቀቅም በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድረስ “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ሴቶች የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ እንዲካሄድ ማዕከላዊ ኮሚቴው ወስኗል፡፡

በመጨረሻም የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከልን  የጎበኙ ሲሆን ከ16 ሺህ 400 ብር በላይ በማዋጣት እና የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለማዕከሉ ማድረጋቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.