Fana: At a Speed of Life!

በረሃማና ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያለባቸውን አካባቢዎች ማልማት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በረሃማና ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያለባቸውን አካባቢዎች ማልማት የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሂደት በቅርቡ እንደሚጀመር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሃመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ከፍተኛ የአየር ንብረት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ በረሃማ ቦታዎችን ያለማችበት መንገድና የቴክኖሎጂ የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሃመድ ÷በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቆላማና በረሃማ የሆኑ አካባቢዎችን ለማልማት የሙከራ ስራዎችን ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን፣ ባለሙያዎችን እና መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሂደት ይጀመራል ብለዋል።

በሚኒስትር ዲኤታው የተመራው ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ከብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ፣ ከተፋሰስ ባለስልጣን፣ ከሰው ሰራሽ አስተውሎ ማዕከል፣ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት፣ ከኢንፎርሜን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችን የያዘ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.