Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ተኮር የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መድረኩን ያዘጋጁት ሰላም ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነው።

የመድረኩ ዓላማ በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን ማረጋገጥ ነው።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው ውይይት ላይ የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።

የመድረኩን አስተባባሪዎች ጨምሮ ከሰሜን ጎንደር፣ ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ ከምዕራብ ጎንደር፣ ከደቡብ ጎንደር፣ ከምዕራብ ጎጃም፣ ከምስራቅ ጎጃም እና ከመተከል ዞኖች እንዲሁም  ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 121 የወረዳ፣ የዞን እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉቀን አየሁ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በሦስት ቀናት በሚኖረው ቆይታም ይህንን ማሳካት የሚያስችል ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።

ተመሳሳይ የውይይት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ስለመሆኑም በመድረኩ መመላከቱን አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.