አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከስዊድንና ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከስዊድንና ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅትም በስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አምባሳደር ኢሪና ሾውልጊን ኒዮኒ እና በኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ እና የምዕራብ አፍሪካ መምሪያ ኃላፊ ለሆኑት ኤሊቤት ሽዋቤ-ሃንሰን በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
አምባሳደሩ ከባለሥልጣናቱ ጋር በተናጠል በበይነ መረብ ባካሄዱት ስብሰባ በብሔራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ድሪባ መንግስት በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ግጭት ላይ የእርቀ-ሰላምን አስፈላጊነት አስገንዝበው ሱዳን ከኢትዮጵያ ግዛት ከወጣች ኢትዮጵያ ለዚህ ዝግጁ መሆኗን አስረድተዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አገልግሎትን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ÷በዚህ ረገድ ሃገራቱ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!