Fana: At a Speed of Life!

የሙለር ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሙለር ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተባቸው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በዛሬው እለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በተሰጠው ክስ መመስረቻ አምስት ቀናት ውስጥ ክስ መመስረቱን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ክሱ በመደበኛ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አምስተኛ የሙስና ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 266478 ክስ መመስረቱን ለችሎቱ ገልጿል፡፡

የአቶ ሙሉጌታ ጠበቆችም ክሱን ለመመልከት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በዛው ችሎት ክሱን የተመለከቱ ሲሆን፥ ክሱ ያልደረሳቸው በመሆኑ ክሱ በዛሬው እለት በተከፈተው መዝገብ እንዲታይላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡

ችሎቱም በጠየቁት መሰረት በተከፈተው መደበኛ ክስ እንዲታይላቸው አዟል፡፡

ይሁንና ከዐቃቤ ህግ ጋር ተማክረው በመደበኛው ችሎት ዳኞች ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በሰኞው መደበኛ ችሎት ጉዳያቸውን ለማየት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በቦሌ ክፍለከተማ ያለአግባብ 50 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት በመውሰድ እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ደግሞ 11 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ወረራ በማድረግ በሚል ሁለት የሙስና ክስ ነው የተመሰረተባቸው፡፡

ይህ ክስ በቀጣይ ሰኞ በመደበኛው ችሎት የሚታይ ይሆናል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.