Fana: At a Speed of Life!

ተመድ እና አሜሪካ በትግራይ ክልል ለሚደረገው የመልሶ ግንባታ እና ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ከመንግስት ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አሜሪካ በትግራይ ክልል ለሚደረገው የመልሶ ግንባታ እና ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ከኢፌዴሪ መንግስት ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን በነበራቸው ውይይት በትግራይ ክልል ለሚያደርገው የመልሶ ግንባታ እና ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ከኢፌዴሪ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጸዋል።

በውይይታቸው ድርጅቱ እና የአሜሪካ መንግስት በበርካታ አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.