Fana: At a Speed of Life!

የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት በቀጣዩ ክረምት ውሃ መያዝ እንዲችል እየተሰራ መሆኑን ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገጭ መስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀ 17ሺ ሄክታር የመስኖ ልማትን ለማከናወን ከማስቻሉም በላይ ለጎንደርና አካባቢው ህብረተሰብም የንፁህ መጠጥ ውሃ እንደሚያስገኝ ተገለጸ።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት በአማራ ብሄራዊ ክልል ጎንደር በመገንባት ላይ የሚገኘውን የመገጭ መስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር በመሆን የመስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃና አጠቃላይ የስራውን ሂደት የተመለከቱ ሲሆን በስራው ላይ ከሚገኙ የግንባታ ባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋርም ውይይት አድርገዋል።

ኮርፖሬሽኑ ሪፎርም ካደረገ በኋላ የተሻለ አፈፃፀም ካሳዩ ፕሮጀክቶች አንዱ የመገጭ መስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በቀጣዩ ክረምት ውሃ መያዝ እንዲችል ለማድረግም እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የግንባታው ሂደት ሳይስተጓጎል በተጀመረው ፍጥነት እንዲጓዝም እንደ ሲሚንቶና ብረት ያሉ ግብዓቶችን እጥረት በመፍታት በኩል ቦርዱ በቅርብ እየተከታተለ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በጉብኝታቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም የወሰን ማስከበር ስራዎች በተሻለ ፍጥነት እየተጠናቀቁ ስራውን የማሳለጡ ተግባር መጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል።

ፕሮጀክቱ ምንም እንኳ በተሻለ አፈፃፀም ላይ ቢገኝም በቀጣይ ይበልጥ እንዲራመድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልፀው የጎንደር ከተማ አስተዳደርም እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንዲቀጥል አስታውሰዋል።

ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ የሚታሰበውን ጥቅም እንዲያስገኝም የሁሉንም አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅም አመልክተዋል።

የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀ 17ሺ ሄክታር የመስኖ ልማትን ለማከናወን ከማስቻሉም በላይ ለጎንደርና አካባቢው ህብረተሰብም የንፁህ መጠጥ ውሃ እንደሚያስገኝ በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.