Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ውይይት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ በሀዋሳ ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ “የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለብልጽግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ መሆኑ ተመላክቷል።

በደቡብ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ ÷ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በአግባቡ የማያስተናግድ የሀገር ግንባታም ሆነ የለውጥ ጉዞ ስኬትና ፍትሃዊ ሊሆን እንደማይችል  ገልጸዋል ።

አያይዘውም የማህበረሰቡን ከ50 በመቶ በላይ የሚይዙትን ሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎና ውሳኔ ሰጭነት፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለሀገሪቱ የለውጥ ስኬት ከፍተኛ ድርሻ አለውም ነው ያሉት።

“ሴቶችን ሳንይዝ ሀገር መገንባትም ሆነ ለውጥ ማምጣት አንችልም ያሉት ወይዘሮ ፋጤ÷ የሀገራችን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሴቶችን ሀሳቦችና ፍላጎቶች በበቂ ሁኔታ ማካተት” እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ሴቶች በሁሉም መስክ የበኩላቸውን ተወጥተው ተሳትፏቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበት እንደሚኖርባቸውያሳሰቡት ሀላፊዋ÷ በተለይ በሰላም ግንባታ ረገድ ቁልፍ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በውይይቱ ከሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ አባላት እየተሳፉ ሲሆን የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከለውጡ በፊትና በሗላ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች በሚል ርዕሰ ጉዳይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.