Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ስቴፋኒ ጆቢን በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ስቴፋኒ ጆቢን በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኔው እንዳስታወቁት፤ በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር እና የአገሪቱ የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ታዛቢ ሆነው እየሰሩ ባሉት አንቶኒ ቼቭሪር ቦታ ስቴፋኒ ጆቢን ተተክተዋል።

እ.አ.አ 1991 ጀምሮ የካናዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም ዓቀፍ ንግድን በህግ ባለሙያነት የተቀላቀሉት ስቴፋኒ ጆቢን የዳበረ ልምድ ያላቸው መሆኑም ተገልጿል።

አምባሳደር ስቴፋኒ ጆቢን በበኩላቸው አገራቸውን ካናዳን በኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ለማገልገል በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ፤ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰሩ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.