ም/ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ህንድ ገብተዋል
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኒው ዴልሂ ህንድ ገብተዋል፡፡
በ4 ቀናት የህንድ የሥራ ጉብኝታቸው ከሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤስ. ጄሻንክራ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በቆይታቸው በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዲፕሎማቶች መኖሪያን ይመርቃሉ፡፡
አቶ ደመቀ ባለፈው ሰኞ በአንካራ ቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ህንፃን መመረቃቸው ይታወሳል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!