Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በመሀል ከተማ ክፍለከተማ በአዲስ አበባ ቀበሌ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

የሐዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የአደጋው መንስኤና የደረሰው የንብረት ውድመት በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዛዡ በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ፣ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም በፀጥታ ኃይሉ ርብርብ አደጋው ወደሌላ አካባቢ ሳይስፋፋ መቆሙንም ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ የመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.