Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ መታወቂያ ስርዓት የመጀመሪያ ቅድመ ትግበራ ሙከራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መታወቂያ ስርዓት የመጀመሪያ ቅድመ ትግበራ ሙከራ መጀመሩን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ሰራተኞችም በመመዝገብ “አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ደረጃ የቅድመ ትግበራ ሙከራውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁንም ነው የገለጸው።

ይህ የተገነባው ስርዓት መሰረታዊ የሆኑትን የግለሰብን የግል መረጃ ሙሉ ስም፣ የትውልድ ዘመን፣ ፆታ፣ ዜግነትና ወቅታዊ የመኖሪያ አድራሻን ይይዛል፡፡

እንዲሁም የባዮሜትሪክ ዳታ ፎቶግራፍ፣ የአስሩም ጣት አሻራና የዐይን ብሌን ያካትታል ተብሏል፡፡

አዲስ የተዘረጋው ስርዓት በማስመሰል የሚደረጉ የተለያዩ ማጭበርበሮችን በአስተማማኝነት ሁኔታ መከላከል እንደሚያስችል ነው የተነገረው።

የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ማንነትን በቀላሉ በመለየት አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋልም ነው የተባለው።

በቀጣይ በአገር አቀፍ ደረጃ ስርዓቱን ለመተግበር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማሟላት ይቻል ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ምክክር እየተደረገበት እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.