የባህርዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በ6ወራት 359ሚሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የባህርዳር ከተማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በ6ወራት 359ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ፡፡
የከተማዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ዋና ስራአስኪያጅ አቶ አለነ መሀሪ እንደገለፁት፤ በ6ወራት 346ሚሊየን 589ሺህ ብር ከወጨና ገቢ ንግድ ፤ከኮንትሮባድ ፣የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ለመሰብሰብ አቅዶ 359ነጥብ 6ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል ፡፡
ከዚህ ውስጥ 59ሚሊየን 650ብር ከውጨ እና 17ሚሊየን 229ሺህ ከገቢ ኮንትሮባንድ፤ በድምሩ 74ነጥብ8ሚሊየን ብር መያዙን አቶ አለነ ገልፀዋል ፡፡
46ሚሊየን 980ሺህ ብር በላይ ደግሞ ከህጋዊ ነጋዴዎች ከንግድ ማጭበርበር የተያዘ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አንስተዋል ፡፡
ከዚህ ባለፈ አብዛኛው ገቢ የተሰበሰበው ከባህርዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያዎች ወረታደረቅ ወደብ ፣ባህርዳር ፣ጎንደር እና መተማ ጣቢያዎች መሆኑን ነው ያስረዱት ፡፡
ከወረታ ደረቅ ወደብ 1ሺህ167 ኮንቴይነሮች የገቡ ሲሆን፤ 940 ኮንቴይነሮች የጉምሩክ ስነስርዓት ተፈፅሞባቸዋል ነው ያሉት አቶ አለነ፡፡
በአጠቃላይ በስድስት 346ሚሊየን 589ሺህ ብር ለመሠብሰብ ታቅዶ 359ነጥብ6ሚሊየን ብር የዕቅዱን 103ነጥብ 5 በመቶ መፈፀሙን ነው የገለፁት፡፡
ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር 225ነጥብ 6ሚሊየን ብር ወይም 169 በመቶ ብልጫ መኖሩን ዋና ስራአስኪያጁ ገልፀዋል ::
የወረታ ደረቅ ወደብ፣ የጉምሩክ ጣቢያዎች በሰው ሀይል ና ግብዓት ማሟላት ፣የፌዴራል እና የክልሉ የፀጥታ ሀይል እገዛ እንዲሁም የማህበረሰቡ ትብብር ለእቅዱ መሣካት ከፍተኛ አሰተዋጽኦ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!