9ኛው የጋምቤላ ክልል አቀፍ የጤና ጉባኤ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛው የጋምቤላ ክልል አቀፍ የጤና ጉባኤ ተጀምሯል፡፡
የክልሉ የጤና ቢሮ ሃላፊ ሮት ጋቶች በክልሉ የጤናውን ዘርፍ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ ንተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አንጻርም በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉና ራሳቸውን እንዲጠብቁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡
በክልሉ የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመቀነስ ከግንዛቤ ማስጨበጥ ጀምሮ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም የወባ ስርጭትን ለመከላከል የአጎበር ስርጭትና የኬሚካል እርጭት ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውን የቢሮው ሃላፊ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ በክልሉ በጤናው ዘርፍ ላገለገሉ የጤና ባለሙያዎችም እውቅና ተሰጥቷል፡፡
በጸጋዬ ንጉስ