Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሕብረት ትምህርት ቤት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በካርቱም የኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ህብረት ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል።
አምባሳደሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከተማሪዎችከመምህራንና አስተዳደር አካላት እንዲሁም ከወላጅ ተወካዮች ጋር ውይይት አደርገዋል።
በዚሁ ጊዜ ተማሪዎቹ የሀገራቸውን ታሪክ፣ባህል እና ቋንቋ በጠበቀ መልኩ መማራቸው ሀገራቸውን እንዳይረሱና ሀገር ወዳድ ትውልድ ሆነው እንዲያድጉ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
ወላጆች እራሳቸውን በማደራጀት በውስን አቅማቸው ልጆችን በትምህርት ለማነፅ የሚያደርጉት ጥረት እጅግ የሚያስመሰግን ተግባር እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
በተጨማሪም ከትምህርት ቤቱ እና ከወላጅ ተወካዮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ውይይት ኤምባሲው ለትምህርት ቤቱ ዕርዳታ በማሰባሰብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
አምባሳደሩም በሱዳን እና በኢትዮጵያ ከሚገኙ መንግስታዊ እና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ኤምባሲው ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥረት እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከኤንባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.