የቡርጂ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል “ወናንካ አያና” ተከበረ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡርጂ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ የቦረና፣ ጉጂ፣ ጌዲኦ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ እና የደራሼ ብሄረሰቦች ተወካዮችም መገኘታቸው ተገልጿል።
በዚህ ወቅት የቡርጂ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር አደም ለሁሉም የብሄሩ ተወላጆች እና ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ÷ብሄረሰቦቹ ለረጅም ዘመናት አብረው የኖሩና የጋራ ታሪክ ያላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ተለያይተው የሚታዩ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የቦረና ፣ጉጂ ፣ጌዲኦ ፣ ኮንሶ ዞኖችና የአማሮ እና የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው በዓሉ የቡርጂ ብሔረሰብ በዓል ብቻ ሳይሆን የኛም በዓል ነው ብለዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪዎቹ የህዝብና የአባገዳዎችን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ለቡርጂ ልማት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ማበርከታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!