Fana: At a Speed of Life!

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤ.ቢ.ሲ) ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

ዩኒቨርስቲው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው በኬሚስትሪና ታሪክ ትምህርት ክፍሎች መምህርና ተመራማሪ ለሆኑት ዶክተር ማዕረግ አማረና ዶክተር ተመስገን ገበየሁ  መሆኑ ተመላክቷል።

በዩኒቨርሲቲው  በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳስታወቀው÷ ለምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ  ነው።

በዚህም በየስራ ክፍላቸው በምርምር፣ ማስተማር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ፕሮጀክት አስተዳደርና በተለያዩ የአመራር ቦታዎች በማገልገል ባበረከቱት አስተዋጽኦ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቀዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ሁለቱ ምሁራን ላስመዘገቡት አስደናቂ ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ  መልዕክትም አስተላልፏል።

ምሁራኑ ወደፊትም  ችግር ፈቺ በሆኑ የምርምር ሥራዎች ፣ በማስተማር እና በማህበረሰብ አገልግሎት መስኮች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑም  ዩኒቨርስቲው ተመኝቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.