Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከመሬት ሊዝ እና ጅምር ግንባታ ጋር በተያያዘ ከ52 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የባከነ ሀብት እየተመረመረ ገቢ እየተደረገ መሆኑን አስታወቁ፡፡

በዚህም በመዲናዋ ከመሬት ሊዝ እና ጅምር ግንባታ ጋር በተያያዘ ለከተማ አስተዳደሩ እንዲከፈል ከተወሰነው ገንዘብ ውስጥ 52 ሚሊየን 747 ሺህ 888 ብር ገቢ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ገንዘቡ በከተማዋ የረጅም ጊዜ የመሬት ሊዝ ዋጋ ያልከፈሉ እና የጅምር ግንባታ መስፈርት ስለማያሟሉ በህጉ መሰረት ተሸጠው ገንዘቡ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢ እንዲሆን ከተወሰነው ከ72 ሚሊየን ብር በላይ ውስጥ የተከፈለ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ቀሪውን 20 ሚሊየን ብርም በውሳኔው መሠረት እንዲፈፅም የፍርድ አፈፃፀም ሂደት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.