የምክር ቤቱ ግምገማ በየመሥሪያ ቤቶቹ የተካሄዱ ዐበይት ክንውኖች የታየበት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባለፉት ስድስት ወራት በእያንዳንዱ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አማካኝነት የተካሄዱ ዐበይት ክንውኖችን መመልከቱን ገለፁ።
አስቻይ ሁኔታዎች፣ ተግዳሮቶች፣ የማኅበራዊ ኃላፊነት እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም በየሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሠራተኞች እና የሥራ ሁኔታን አጣጥሞ ምቹ የሥራ ከባቢ ከመፍጠር አንጻር የተከናወኑ ሥራዎች መፈተሻቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የጋራ ኃላፊነት በሚስተዋልባቸው መስኮች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በተሻለ ቅንጅት መሥራታቸው፣ መንግሥት በተሻለ የማስተባበር ሚናን መወጣቱ፣ ሂደቶችን መሠረታዊ እና የተቀላጠፈ ማድረግ እና የፈጠራ ባህልን ማዳበር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በመንግሥት መዋቅር እና ተቋማት ዙሪያ፣ እንዲሁም ከመንግሥት ወደ ኅብረተሰቡና ወደ ግሉ ዘርፍ የመረጃ ፍሰት እንዲሳለጥ ማድረግ እንዲሁም የሕዝቡን ፍላጎት በተቀላጠፈ የአገልግሎት አሰጣጥ አማካኝነት ምላሽ ለመስጠት የሚቻልባቸውን መንገዶች ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!