Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና ህዝብ 15 ሚሊየን ብር ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና ህዝብ ማጠናከሪያ የሚሆን 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን ያበረከቱት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ድጋፉ መንግስት በትግራይ ክልል ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ወቅት ጉዳት ለደረሰበት የትግራይ ክልል ህዝብ ማጠናከሪያ ሲሆን ከገንዘቡ በተጨማሪ አንድ አምቡላንስና አንድ ፓትሮል መኪናም ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለመስጠት መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡

አቶ ደስታ አያይዘውም የሚገጥሙንን ፈተናዎች እርስ በእርስ ተደጋግፈን መሻገር ካልቻልን ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ እክል ይፈጥርብናል ብለዋል፡፡

ድጋፉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ተረክበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.