ቻይና መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርገውን እርዳታና መደበኛ ህይወት ወደነበረበት እንዲመለስ የሚያደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለተጎጂዎች የሚያደርገውን እርዳታና በክልሉ መደበኛ ህይወት ወደነበረበት እንዲመለስ የሚያደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ሃገራቸው በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡
በዚህም በክልሉ ለተጎዱ ዜጎች ዱቄት እና ሩዝን ጨምሮ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድፍፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል፡፡
ቃል አቀባዩ መላው ኢትዮጵያውያን የሃገሪቱ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና እንደሚያስደስታቸው እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ቻይናም መንግስት በትግራይ ክልል ለተጎጂዎች የሚያደርገውን እርዳታና በክልሉ መደበኛ ህይወት ወደነበረበት እንዲመለስ የሚያደርገውን ጥረት ትደግፋለችም ነው ያሉት፡፡
አያይዘውም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሻለ ድጋፍ እንዲያደርግና የቀደመው መደበኛ ህይወት ወደነበረበት እንዲመለስ በቅንጅት እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን