Fana: At a Speed of Life!

ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውል መድኃኒት እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውል በቂ መጠን ያለው መድኃኒት እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅርቦት ኤጀንሲው ለስኳር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችን ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ካለው የፍጆታ መጠን አንፃር በቂ የሆነ መድሀኒት ማሰራጨት መጀመሩን የስርጭት ባለሞያ ወ/ሪት ምህረት ጌታሁን አስታወቁ።

መድሀኒቶቹም ኢንሱሊን ሶሉብል እና ኢንሱሊን አይሶፌን ባይፌዚክ ሚክስቸር ናቸው።

ለስኳር በሽታ ደረጃ 1 እና 2 ህሙማን እንዲሁም ከስኳር ህመም ጋር ተያይዘው ለሚከስቱ የጤና እክሎች የሚውሉ መድኃኒቶች መሆናቸውን ባለሙያዋ አብራርተዋል።

የመድኃኒት ስርጭቱም በሁሉም ቅርንጫፎች አማካኝነት ለጤና ተቋማት እየተካሄደ ሲሆን 12 ሚሊዮን 72 ሺህ 679 ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ለስኳር ታካሚዎች የሚሆን በቂ መድሀኒት ያለ ሲሆን እየተሠራጨ በመሆኑ ህብረተሰቡ እጥረት አለ ብሎ መጨናነቅ አንደሌለበት ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.