Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ከጀርመን እና ከፖላንድ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ከጀርመን እና ከፖላንድ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ሙሉ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ የሰብ ሰሀራ አፍሪካ እና ሳሄል ዳይሬክተር አምባሳደር ሮበርት ዶግለር ጋር ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና ስለ ሁለትዮሽ ጎዳዮች በስልክ ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩም አምባሳደሮቹ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አምባሳሯ በፖላንድ የአለም አቀፍ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ፕሮግራም ኃላፊ ዶክተር ካሮል ዋሲለውስኪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በቪዲዮ ባካሄዱት ውይይት አምባሳደር ሙሉ ስለወቅታዊ ጉዳዮች፣ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ሂደት እና አሁናዊ ሁኔታ እና ስለ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ካሮል ዋሲለውስኪ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ማብራሪያ አመስግነው ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.