ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶች እና የልብስ ቦንዳ በህገወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 16 ሚሊየን 63 ሺህ 250 ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶች እና የልብስ ቦንዳ በህገወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ በቱሉ ዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተያዘ፡፡
መድሃኒቱና የልብስ ቦንዳው የካቲት13 ቀን ሌሊት ላይ በተደረገ ፍተሻ የተያዘ ነው፡፡
የመኪናው አሽከርካሪ እህል የጫነ በማስመሠል መድሃኒቶቹን እና የልብስ ቦንዳውን ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት መሞከሩን የቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ዋርዮ ጉዮ ተናግረዋል፡፡
መድሃኒቶቹ ወጣቶች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡