Fana: At a Speed of Life!

ቀጣዩ ምርጫ በብሔራቸው ከተሰየመ ክልል ውጪ የሚኖሩ ዜጎችን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ሊካሄድ ይገባዋል -የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀጣዩ ምርጫ በብሔራቸው ከተሰየመ ክልል ውጪ የሚኖሩ ዜጎችን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ሊካሄድ ይገባዋል አለ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፡፡

የመማክርት ጉባኤው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፡ ከክልላቸው ውጪ የሚኖሩ ዜጎች በመራጭነትም በተመራጭነትም የሚሳተፉበትን አስቻይ ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል ብሏል፡፡

ለዚህም በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስተዳደር ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች አስፈላጊውን ሁሉ ሊያደርጉ ይገባል ሲል የመማክርት ጉባኤው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የክልል ምክር ቤቶች እውነተኛ የህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝምን የሚያንጸባርቁ እንዲሆኑ መስራት ይገባልም ብሏል የመማክርት ጉባኤው በመግለጫው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.