Fana: At a Speed of Life!

4 ሺህ 320 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እጽ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጉሙሩክ ኮሚሽን 4 ሺህ 320 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እጽ መያዙን አስታወቀ፡፡
እጹ የተያዘው በኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ተጭኖ ከሻሻመኔ ወደ ሞያሌ ሲጓጓዝ መሆኑ ታውቋል፡፡
የአደንዛዥ እጹ ግምታዊ ዋጋም ከ17 ሚሊየን ብር በላይ እንደሆነም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርንጫፍ የጪጩ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስተባባሪ ኮማንደር ጫላ ቡልቻ እንደገለጹት አደንዛዥ እጽን ሲያጓጉዝ የነበረው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሏል።
መቆጣጠሪያ ጣቢያው ጥቆማ ደርሶት ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ያወሱት አስተባባሪው፤ አሽከርካሪው የሰሌዳ ቁጥሩን በመቀየር አጭበርብሮ ለማለፍ ሙከራ ማድረጉን መግለፃቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.