በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ ለወጣባቸው ቤቶችን ለባለ ዕድለኞች የቁልፍ ርክክብ መሰጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ የወጣባቸው እና የግንባታ አፈጻጸማቸው የተሻሉትን ቤቶችን ለባለ ዕድለኞች የቁልፍ ርክክብ መሰጠት ተጀመረ ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መስከረም ዘውዴ በሀያት 49 ማዞሪያ ሳይት በመገኘት የቤቶቹን ቁልፍ ለባለዕድለኞች አስረክበዋል ።
የአዲስአበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በየቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ባለዕድለኞች የቤቶቹን ቁልፍ እንደሚያስረክብ መገለፁን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
በሁለተኛው ዙር ዕጣ ከወጣባቸው 11 ሳይቶች የግንባታ ስራቸው ከ220 ህንፃዎች ቁልፋቸውን የሚረከቡ ባለ ዕድለኞችንም የቤቶቹን ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ማሰራት የሚትችሉ መሆኑን በቁልፍ ርክክብ መርሐግብር ላይ ተጠቁሟል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!