Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ለ 928 ወጣቶችና ሴቶች የመስሪያ ቦታ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለ928 ወጣቶችና ሴቶች የመስሪያ ቦታ ሸዶችን በእጣ አስተላለፈ፡፡
የመስሪያ ሼዶቹን የአዲስ አበባ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለም እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባወይ ዮሃንስ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ አንቀሳቃሾች አስረክበዋል፡፡
በክፍለ ከተማው የመስሪያ ቦታ ከተረከቡት 928 ሴቶችና ወጣቶች መካከል 543ቱ በልብስ ስፌት 210 በእንጨትና ብረታ ብረት፣120ዎቹ በሸክላ ስራ፣30 በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 25 በደረቅ ምግብ ዝግጅት የስራ ዘርፎች የተሰማሩ መሆናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.