የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቁን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ በትናንትናው ዕለት መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
የእጩዎችን ምዝገባ በሁለት ዙር ማካሄዱን ያስታወሰው ያስታወሰው ቦርዱ በተለያዩ ምክንያቶች ተጨማሪ ቀናት በመጨመር እና የፓርቲዎችን አቤቱታዎች በመፍታት ሲያከናውን መቆየቱንም ገልጿል፡፡
ቦርዱ በጸጨማሪም በቢሮዎች ችግር የተነሳ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ካልሆነ በስተቀር ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ በይፋ መዘጋቱን ነው የጠቀሰው፡፡
በተጨማሪም አጠቃላይ የጸደቁ የእጩዎች ዝርዝርን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግም ነው ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ከየካቲት ስምንት ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሄድ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!