Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ ዛሬ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀጣይነት ላለው የሃገር እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚዳሰስበት ነው ተብሏል፡፡
እንዲሁም ጉባኤው በአባል ሃገራቱ ላይ እየተስተዋሉ ስለሚገኙ የዜጎች ስደት እና መፈናቀል የሚመክር ሲሆን የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከፍተውታል።
ጉባኤው ከአባል ሃገራቱ የተውጣጡ 20 ዩኒቨርሲቲዎች እየተሳተፉ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ የሶማሌ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
መድረኩ ከታለመለት ዓላማ አንዱ የኢጋድ የትምህርት እድል እና የሽልማት መርሃ ግብር ማዘጋጀት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ዛሬ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከአራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በመድረኩ የኢጋድ የነፃ ትምህርት እድል ፕሮግራም ተጀምሯል፡፡
በተጨማሪም ከአባል ሃገራት የተውጣጡ ዩኒቨርሲቲዎች አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
በዚህም የካርቱም ዩኒቨርሲቲ ለ 2020/21 የትምህርት ዘመን የ200 ነጻ የትምህርት እድል ቃል ገብቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.