Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ለሴቶችና ለህጻናት ማዕከልና ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትኩረት ለሴቶችና ለህጻናት ማዕከል እና ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ከተማ አስተዳደሩ ለትኩረት ለሴቶችና ለህጻናት ማህበር ለሴቶችና ለህጻናት ማህበር 200ሺህ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ደግሞ 578ሺህ ብር የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አድርጓል ።
በተጨማሪም ሴንቸሪ ግሩፕ ካምፓኒ ለሁለቱም በጎ አድራጎት ማህበራት ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለሁለቱም ማዕከላት የተቋም መገንቢያ የሚሆንና በከተማ አስተዳደሩ የተወሰነላቸውንም የቦታ ፍቃድ ይፋ አድርገዋል ።
ወይዘሮ አዳነች ከራስ በላይ ለሌሎች መኖርን በተግባር ያላሳዩን እነዚህ በጎ አድራጎት ማህበራት እውነተኛ እራስን የመስጠት ፍቅር ስላደረጉ ምስጋና ይገባቸዋ ብለዋል ።
በቀጣይም የአዕምሮ ህመምተኞች እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ በሚደረገውን ጥረት በመሰል በጎ አድራጎት ስራ ለተሰማሩ ተቋማት ቅን ባለሀብቶችን እና በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦችን በማስተባበር የተለያዩ ድጋፎችን የሚያገኙበት መንገድ እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባዋ ማመላከታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.