Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የከተማ ግብርናን ለማሳደግ በአዲሱ ቅጥር ግቢው ውስጥ እያከናወነ የሚገኘውን ሥራ ጎብኝተዋል፡፡

በኤጀንሲው የተዘጋጀው የቀጥተኛ እርሻ ናሙና ሌሎች ተቋማት እና ቤተሰቦች ቢጠቀሙበት በከተማ ግብርና አማካኝነት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፡፡

በተጨማሪም ከተሞች ቢያንስ በከፊል ራሳቸውን መመገብ አለባቸውም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.