ቢሮው በመዲናዋ ለተሰማሩ ነጋዴዎችና የንግድ አደረጃጀት ዘርፎች እውቅናና ሽልማት ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በመዲናዋ ለተሰማሩ ነጋዴዎችና የንግድ አደረጃጀት ዘርፎች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
እውቅናና ሽልማቱ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ስራ የሰሩ፣ ህገወጥን ንግድን የተከላከሉና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓትን የተከተሉ ነጋዴዎችን ለማበረታታት የተደረገ ሰለመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱል ፈታህ የሱፍ ተናግረዋል።
የንግድነና ኢንደስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በስነስርዓቱ እንደተናገሩት፥ በሀገራችን ካሉ 2ነጥብ 4ሚሊየን የንግድ ደርጅቶች ከ632 ሺህ በላይ የሚሆኑት በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡
በዚህም ነጋዴዎችና የንግድ አደረጃጀት ዘርፎች በህጋዊ የንግድ ስርዓት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ በሀገራችን የምጣኔ ሀብት ግንባታ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም ነው የተናገሩት።
ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለማስፈንና የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ከንግድ ማህበረሰብ ጋር የተሻለ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ መላኩ ተናግረዋል።
በንግድ ስርዓቱ ያለውን ህገወጥነት እየተከላከሉ ህጋዊ ነጋዴዎችን ማመስገንን እና እውቅና መስጠት የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በጌታሰው የሽዋስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!