የአሜሪካ ተቋማት በኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ ዴቪድ ሬንዝ ከተመራ የሴኔቱ ተመራጭ የደህንነት ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ተቋማቶቻቸው በጋራ መስራት በሚችሉባቸውና ዘርፉ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ በሚኖረው አስተዋፅኦ ዙሪያ መክረዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከአሜሪካ ጋር የመስራት ፍላጎት አላት ያሉ ሲሆን የአሜሪካ ተቋማት በኢትዮጵያ ማዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ ዴቪድ ሬንዝ በበኩላቸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የአሜሪካ ተቋማት በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
.